Homeመነሻ ገጽ / Hall Rentalየአዳራሽ ኪራይ

Event Hall Rental in Richmond, VA

የአዳራሽ ኪራይ በሪችመንድ፣ ቨርጂኒያ

A hall for up to 400 guests, with a kitchen, tables and chairs. For weddings, christenings, birthdays, memorials, graduations and community gatherings.

እስከ 400 እንግዶችን የሚያስተናግድ፣ ወጥ ቤት፣ ጠረጴዛና ወንበር ያለው አዳራሽ። ለሠርግ፣ ለክርስትና፣ ለልደት፣ ለተዝካር፣ ለምረቃና ለማኅበረሰብ ስብሰባዎች።

The hallአዳራሹ

Room for your whole community

ለመላው ማኅበረሰብዎ የሚበቃ ቦታ

Our event hall at 2210 Carter St in Richmond is open to church members, non-members and approved outside organizations. Tables, chairs and the kitchen are on site, so you only need to bring your food, plates and decorations.

በ2210 ካርተር ስትሪት፣ ሪችመንድ የሚገኘው አዳራሻችን ለቤተ ክርስቲያኑ አባላት፣ አባል ላልሆኑና ለተፈቀደላቸው ድርጅቶች ይከራያል። ጠረጴዛ፣ ወንበርና ወጥ ቤት ስላለ ምግብዎን፣ ሳህኖችንና ማስጌጫዎችን ብቻ ይዘው ይምጡ።

400guests, maximumከፍተኛ የእንግዶች ብዛት
53round & rectangular tablesክብና አራት ማዕዘን ጠረጴዛዎች
11 PMevents end byዝግጅቶች የሚያበቁበት
  • Full kitchen: refrigerator, stove, microwave, dishwasher
  • Folding and stacking chairs
  • 17 round and 36 rectangular tables
  • Restrooms at the front entrance
  • Projector screen (add-on)
  • Tablecloths, chair covers, runners (add-on)
  • 1 hour setup + 1 hour cleanup included
  • On-site and street parking
  • ሙሉ ወጥ ቤት፦ ማቀዝቀዣ፣ ምድጃ፣ ማይክሮዌቭ፣ ዕቃ ማጠቢያ
  • ወንበሮች
  • 17 ክብና 36 አራት ማዕዘን ጠረጴዛዎች
  • በዋናው መግቢያ ያሉ መጸዳጃ ቤቶች
  • የፕሮጀክተር ስክሪን (በተጨማሪ ክፍያ)
  • የጠረጴዛ ልብስ፣ የወንበር ልብስ (በተጨማሪ ክፍያ)
  • 1 ሰዓት ለዝግጅት + 1 ሰዓት ለጽዳት ተካቷል
  • በግቢው ውስጥና በመንገድ ላይ ማቆሚያ
Inside the Debre Enqu Beata LeMariam event hall in Richmond, VA, set with round tables, white linens, chairs and chandeliers for a reception
Ratesዋጋ

Rental fees

የኪራይ ክፍያ

Rates are set by the number of guests and whether you use the kitchen. The security deposit is refunded within 7–10 business days after the event if the hall is returned clean and undamaged.

ዋጋው በእንግዶች ብዛትና ወጥ ቤት በመጠቀምዎ ይወሰናል። አዳራሹ ንጹሕና ጉዳት ሳይደርስበት ከተመለሰ፣ የዋስትና ገንዘቡ ከዝግጅቱ በኋላ በ7–10 የሥራ ቀናት ውስጥ ይመለሳል።

Guestsእንግዶች Depositዋስትና With kitchenከወጥ ቤት ጋር Without kitchenያለ ወጥ ቤት
Up to 50እስከ 50$255$850$350
Up to 100እስከ 100$300$1,000$500
Up to 200እስከ 200$525$1,750$1,250
Up to 300እስከ 300$675$2,250$1,750
Up to 400 (max)እስከ 400 (ከፍተኛ)$750$2,500$2,000

Discountsቅናሾች

  • Priests and deaconsካህናት እና ዲያቆናትFreeበነጻ
  • Debre Enqu Beata LeMariam membersየደብረ ዕንቁ በዓታ ለማርያም አባላት25% off25% ቅናሽ
  • Non-members and organizationsአባል ያልሆኑና ድርጅቶችFull priceሙሉ ዋጋ

Optional add-onsተጨማሪ ዕቃዎች

ItemዕቃPriceዋጋ
Projector screenየፕሮጀክተር ስክሪን$75
Tablecloth (round or rectangular)የጠረጴዛ ልብስ (ክብ ወይም አራት ማዕዘን)$7 each$7 በአንዱ
Table runnerየጠረጴዛ ሯጭ$3 each$3 በአንዱ
Spandex chair coverየወንበር ልብስ$1 each ($0.75 for 100+)$1 በአንዱ (ከ100 በላይ $0.75)
How to bookእንዴት እንደሚያዝ

From request to event day

ከጥያቄ እስከ ዝግጅቱ ቀን

Send a request with the form below. Dates are first come, first served, up to 6 months ahead.ጥያቄ ይላኩ ከታች ባለው ቅጽ። ቀናት የሚያዙት ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ በመስጠት ነው፤ እስከ 6 ወር አስቀድሞ።

We confirm availability and hold the date for 48 hours while you sign the agreement.ቀኑ መኖሩን እናረጋግጣለን፤ ውሉን እስኪፈርሙ ድረስ ቀኑን ለ48 ሰዓት እንይዛለን።

Sign and pay at least 30 days before: two checks to “Debre Enqu Beata LeMariam Cathedral EOTC”, one for the fee and one for the deposit. Bring them in or mail them to 2210 Carter St, Richmond, VA 23222. Online payment is opening soon.ይፈርሙና ይክፈሉ ቢያንስ ከ30 ቀን በፊት፦ ለ“Debre Enqu Beata LeMariam Cathedral EOTC” የሚጻፉ ሁለት ቼኮች፤ አንዱ ለኪራይ፣ አንዱ ለዋስትና። በአካል ያምጡ ወይም ወደ 2210 Carter St, Richmond, VA 23222 በፖስታ ይላኩ። የኦንላይን ክፍያ በቅርቡ ይጀመራል።

7 days before: send a $1M event liability insurance certificate and meet the hall coordinator.ከ7 ቀን በፊት፦ የ$1 ሚሊዮን የዝግጅት ኢንሹራንስ ሰርተፊኬት ያቅርቡና ከአዳራሹ አስተባባሪ ጋር ይገናኙ።

After the event, clean up using the checklist. Your deposit comes back within 7–10 business days.ከዝግጅቱ በኋላ በዝርዝሩ መሠረት ያጽዱ። ዋስትናዎ በ7–10 የሥራ ቀናት ይመለሳል።

Good to knowማወቅ ያለብዎት

Hall rules

የአዳራሹ ደንቦች

Breaking these rules can mean losing your security deposit. The full terms are in the rental agreement.

እነዚህን ደንቦች መጣስ የዋስትና ገንዘብን ሊያሳጣ ይችላል። ሙሉ ዝርዝሩ በየኪራይ ውሉ ውስጥ ይገኛል።

No alcohol or smokingመጠጥና ማጨስ የተከለከለ ነው

Anywhere on church property, including the parking lot.

በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ በሙሉ፣ መኪና ማቆሚያውን ጨምሮ።

Ends by 11 PMእስከ ምሽቱ 5 ሰዓት (11 PM)

Guests leave by 11 PM; cleanup only until midnight.

እንግዶች እስከ 11 PM ይወጣሉ፤ ከዚያ እስከ እኩለ ሌሊት ጽዳት ብቻ።

Setup and cleanupዝግጅትና ጽዳት

One hour before and after is included. Extra time is billed hourly.

ከዝግጅቱ በፊትና በኋላ አንድ ሰዓት ተካቷል። ተጨማሪ ጊዜ በሰዓት ይከፈላል።

Decorationsማስጌጫዎች

No tape, nails, tacks, staples, hot glue, confetti or glitter. Ask for written approval for items other than tables and chairs.

ፕላስተር፣ ሚስማር፣ ስቴፕለር፣ ሙጫ፣ ኮንፈቲ ወይም ብልጭልጭ አይፈቀድም። ከጠረጴዛና ወንበር ውጭ ላሉ ዕቃዎች የጽሑፍ ፈቃድ ይጠይቁ።

Bring your own suppliesየራስዎን ዕቃ ይዘው ይምጡ

Plates, cups, utensils and cleaning supplies are provided by the renter.

ሳህን፣ ኩባያ፣ ማንኪያና የጽዳት ዕቃዎችን ተከራዩ ያቀርባል።

Childrenልጆች

Anyone under 16 must be with an adult at all times.

ከ16 ዓመት በታች ያሉ ሁልጊዜ ከአዋቂ ጋር መሆን አለባቸው።

Parkingመኪና ማቆሚያ

Use street parking once the church lot is full. Keep the daycare entrance next door clear.

የቤተ ክርስቲያኑ ማቆሚያ ሲሞላ በመንገድ ላይ ያቁሙ። የአጠገቡን የሕፃናት ማቆያ መግቢያ አይዝጉ።

Hall onlyአዳራሹ ብቻ

The sanctuary and rooms next to it are not part of the rental.

ቤተ መቅደሱና አጠገቡ ያሉ ክፍሎች በኪራዩ ውስጥ አይካተቱም።

No sales eventsየንግድ ዝግጅት አይፈቀድም

Meetings and conferences are welcome, but no selling or fundraising for profit.

ስብሰባና ጉባኤ ይፈቀዳል፤ ሽያጭ ወይም ለትርፍ የሚደረግ ዝግጅት ግን አይፈቀድም።

Cancellation policyየስረዛ ደንብ

If you cancelከሰረዙRental feeየኪራይ ክፍያDepositዋስትና
60+ days beforeከ60 ቀን በፊትFull refund minus $50 admin fee$50 ተቀንሶ ሙሉ በሙሉ ይመለሳልRefundedይመለሳል
30–59 days beforeከ30–59 ቀን በፊት50% refunded50% ይመለሳልRefundedይመለሳል
15–29 days beforeከ15–29 ቀን በፊት25% refunded25% ይመለሳልRefundedይመለሳል
Less than 15 daysከ15 ቀን ያነሰNo refundአይመለስምRefundedይመለሳል

You can reschedule at no charge with at least 30 days’ notice if the new date is open. If the church has to cancel, you receive a full refund.

ቢያንስ 30 ቀን አስቀድመው ካሳወቁና አዲሱ ቀን ክፍት ከሆነ ያለ ክፍያ ቀን መቀየር ይችላሉ። ቤተ ክርስቲያኑ ዝግጅቱን ከሰረዘ ሙሉ ገንዘብዎ ይመለሳል።

Request a dateቀን ይጠይቁ

Hall rental request

የአዳራሽ ኪራይ መጠየቂያ

This is a request, not a booking. The church office will contact you to confirm availability and send the agreement.

ይህ ጥያቄ እንጂ ማረጋገጫ አይደለም። ጽሕፈት ቤቱ ቀኑ መኖሩን አረጋግጦ ውሉን ይልክልዎታል።

Your detailsየእርስዎ መረጃ
Your eventዝግጅትዎ
Maximum 400ከፍተኛው 400
No later than 11:00 PMከ11:00 PM ያልበለጠ
What you needየሚያስፈልግዎ
Kitchenወጥ ቤት
Add-onsተጨማሪ ዕቃዎች

Questions? Callጥያቄ ካለዎት ይደውሉ፦ 703-364-8452 · 571-376-0826 · [email protected]